CERS-Bureau of Agriculture
የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት የሆሳዕና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግብርና ናሙና ቆጠራ ዙሪያ ከክልሉ ግብረ ሀይል ጋር የግንዛቤ መፍጠሪያ ምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ አቶ ኡስማን ሱሩር በምክክር መድረኩ እንደገለጹት ትክክለኛ መረጃ ለትክክለኛ ውሳኔ መሰረት ነው ብለዋል።
በሀገራችን የግብርና ነሙና ቆጠራ ከተካሄደ ረጅም ጊዜ ማስቆጠሩን በመግለፅ ይህ ተግባር ለኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተግባራት ወሳኝ ነው ብለዋል።
የግብርና ናሙና ቆጠራ ዋና ዓለማው የሰብል፣ የእንስሳት ሀብት እና የመሬት አጠቃቀም መረጃ ለመሰብሰብ ብሎም ለበጀት አጠቃቀም የሚረዳ እንደሆነም ገልፀዋል ።
በኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት የሆሳዕና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን አሰፋ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በትክክለኛ ልማት ዕድገት ላይ በመሆኑ ትክክለኛ መረጃ ያስፈልጋል ብለዋል።
የግብርና ናሙና ቆጠራ አስፈላጊውን መረጃ ለሚመለከታቸው አካላት በማቅረብ እና ለፖሊሲ ብሎም ለስትራቴጂ ስራዎች የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ገልፀዋል።
በመድረኩም የክልል፣ የዞን እና የልዩ ወረዳዎች የግብርና ናሙና ቆጠራ ግብረሃይል አባላት ተሳትፈዋል።
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU