• Call Us
  • +25146 554 16 87

ፕሮጀክቶች

                                   የእንስሳት እና አሳ ሀብት ሴክተር ልማት ፕሮጀክት (LFSDP)

የእንስሳት እና አሳ ሀብት ሴክተር ልማት ፕሮጀክት በመንግስት የተያዙ ዕቅዶችን ለማሳካት የሚሰራ መንግስታዊ ፕሮጀክት ነዉ፡፡ ፕሮጀክቱ በክልላችን በተመረጡ አስር ወረዳዎች በተለዩ አራት የእንስሳትና አሳ ዘርፍ እሴት ሰንሰለቶች ማለትም በወተት፣ በዶሮ፣ በቀይ ስጋና በኣሳ ሀብት ልማት ላይ ተቀርፆ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተግባር በመግባት እየሰራ  የሚገኝ ፕሮጀክት ነዉ፡፡

ፕሮጀክቱ  በዋናነት በአለም ባንክ የሚደግፍ ሲሆን አምራቾችና ምርት አቀናባሪዎችን የማምረትና የግብይት ትስስር ማጠናከር፣ የእንስሳትና አሳ ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥን ማቀላጠፍ፣ የዘርፉን የአደጋ ተጋለዐጭነት ስጋት መቀነስ እንዲሁም ፈጣን ምላሽ በመስጠት በሚሉት ሶስት ዋና ዋና የዘርፉን ዓላማዎች ለማሳካት ይሰራል፡፡

የአምራች  አርሶ አደሮችን የገበያ ትስስር ማጠናከር፣ የዘርፉን ተቋማትና የልማት ፕሮግራሞች ማጠናከር እንዲሁም የፕሮጀክት ስራዎችን ማስተባበር ክትትልና ግምገማ ስራዎችን የሚመለከቱ ሶስት ዋና ዋና አምዶች የትኩረት መስኮች በማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

                                    የዘላቂ የመሬት አስተዳደር ፕሮግራም 3 (SLMP III)

የዘላቂ የመሬት አስተዳደር ፕሮግራም በተመረጡ የክልሉ ወረዳዎች የሚገኙ አነስተኛ ንዑስ ተፋሰሶች ዉስጥ የተለዩ  የተጎዱ መሬቶችን መልሶ በማልማት የአየር ንብረት ዉጦችን ተግዳሮቶች ለመቋቋም እንዲችሉ፣ ምርትና ምርታመነታቸዉን እንዲያሻሽሉ፣ የካርበን አማቂ ጋዞችን እንዲያምቁና በልዩ ልዩ የኑሮ አማራጮች ሕይወታቸዉን እንዲለዉጡ ለማስቻል ተቀርፆ በመተግበር ላይ የሚገኝ ፕሮግራም ነዉ፡፡

ፕሮግራሙ  በመጀመሪያና በሁለተኛዉ ምዕራፎች ተግባሩን ሲያከናዉን የቆየና በሶስተኛዉ ምዕራፍ የቀጠለ ሲሆን አረንጓዴ ልማት እና ተግዳሮትን የሚቋቋም ሕብረተሰብ መገንባት፣ የአየር ንብረት ለዉጥን የሚቋቋም መረጃና ተቋማዊ አቅም መገንባት፣ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓትን ማጠናከርና የፕሮግራም ስራ አመራና መረጃ ልዉዉጥ ስርዓትን ተግባራዊ የማድረግ ስራዎችን ማከናወን የፕሮግራሙ አበይት የትኩረት መስኮች ናቸዉ፡፡