• Call Us
  • +25146 554 16 87

የእርሻ ልማት ዘርፍ

                                 በቢሮ ም/ሀላፊ የሚመራ የእርሻ ልማት ዘርፍ ተጠሪነቱ ለግብርና ቢሮ ሀላፊ ሆኖ የሚከተለውን ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡-

O የእርሻ ልማት ዘርፍ ምርታማነት ለማሻሻል ለአርሶ አደሩ፣ ለግል ባለሀብቱና በሰብል ልማት ለተሰማሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጡ የኤክስቴንሽንና የስልጠና   አገልግሎት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤

O የአየር ንብረት ለውጥ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ተመጋጋቢነት እንዲጎለብት ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታታላል፣ ይመራል፤

O ስነ-ምህዳርና ከባቢ አየርን መሠረት ያደረጉ የግብርና አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን በሰብል አመራረት ስርዓቱ ውሰጥ ውጤታማነትና ዘላቂ ልማት በሚያረጋግጥ   መልኩ እንዲተገበሩ ያደርጋል፣ በዘርፋ የሚሰሩ አካላትንም ይደግፋል፣

O የመነሻ ዘር ብዜትን ያስተባብራል፣ ስርዓቶችን ያዘጋጃል ተግባራዊ ያደርጋል፣ እንዲሁም የዘር ብዜት ሥራ የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኝ ያደርጋል፣

O የአየር ንብረት መረጃን መሠረት ያደረገ የሰብል ልማት ምክረ ሀሳብ በዘመናዊና ተደራሽ በሆነ መልኩ ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ ያደርጋል፤

O የምርት ብክነትን ለመቀነስ እና የምርት ጥራትን ለማሻሻል የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮችን ይለያል፣ የምርምር ስራዎች እንዲሰሩ ይደግፋል፣ ለአርሶ አደሩና   ለግል ባለሀብቱ እንዲደርሱ ያደርጋል፣ ውጤታማነታቸውን ይገመግማል፤

O የመደበኛ ተባዮች ጉዳትን ለመቀነስ የሚረዱ ከዘር ጀምሮ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ከባቢ አየርን በማይጎዳ መልኩ ተደራሽ ያደርጋል፤

O ዘርፍን ለማዘመን የሚረዱ ዕውቀትና ክህሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ ስልጠናዎች ይለያል፣ የአጭርና የረጅም ጊዜ አቅም ግንባታዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፣   ይመራል፤

O ለዘርፉ ልማት ምርታማነትና ዕድገት ዘለቄታዊ ልማት አጋዥ የሆኑ ስትራቴጂዎችንና አቅጣጫዎችን በማሳየትና በማዘጋጀት የሀብት ምደባ በማመቻቸት የቁጥጥርና ክትትል ድጋፎችን በማድረግ የግብርናን ይመራል፤

O ለዕቅድና ለውሳኔ አሰጣጥ ድርሻ ያላቸውን የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት መረጃዎች ከባለደርሻ አካላት ጋር በመሆን ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፤

O የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ግቦችን ሊያሳኩ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን፣ፓኬጆችንና አሰራሮችን ይለያል፣ ይመርጣል፣ ቴክኖሎጂዎችና   የመፍትሄ ሀሳቦች በኤክስቴንሽን ስርዓቱ እንዲስፋፉ ይመራል፣ ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፤

O ዘርፉ ከስሩ የሚከተሉት ዳይሬክቶሬቶች ያስተባብራል፡-

                    o. የሰብል ልማት ዳይሬክቶሬት

                    o. የሆርቲካልቸር ልማት ዳይሬክቶሬት

                    o. የእርሻና ሆርቲካልቸር ኤክስቴንሽን ዳይሬክቶሬት