CERS-Bureau of Agriculture
የቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ተጠሪነቱ ለግብርና ቢሮ ሀላፊ ሆኖ የሚከተለው ተግባርና ኃፊነት ይኖረዋል፡-
O መንግስት የወጡ ልዩ ልዩ የልማትና የምርምር ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች አፈጻጸም ዝርዝር ጥናት እያጠኑ ከተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት አንጻር በመገምገም ቢሮ ሀላፊው ያማክራሉ፤
O ስለ መንግስት የስራ አመራር እና ተቋሚ ለውጥ የሚወጡ ደንቦችና መመርያዎች በመተንተን የተቋሙ የሀብት ሥራ አመራር የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማሣደግና ለማሻሻል የሚያችል ጥናት ያካሄዳሉ፣
O የመ/ቤቱን ስትራቴጂክና ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም የተሻለ አፈጻጸምና ውጤት ለማስመዝገብ እንዲቻል ከውስጥና ከሌላ ተሞክሮ በመቀመር የተሻለ አቅጣጫ ለመከተል የሚያስችል ሂደት ሀላፊው ያማክራሉ፣ ይደግፋሉ፣
O በተቋሙ አፈጻጸም ዙሪያ የውስጥ ህጎችን፣ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን፣ መመሪያና ከደንቦች ጋር በማገናዘብ ያማክራሉ፤ ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮችን በመለየት ከአስተያየት ጋር ያቀርባሉ፤
O ፖሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ህጎች ላይ ጥልቅ ትንተና ያደርጋሉ፤
O ቢሮ ሀላፊው በፕሬስ ሪሊዝ፣ ፕሬስ ኮንፍረንስ፣ በቃለ ምልልስ፣ በሚዲያ በሚያስተላልፈው መግለጫዎች ላይ አስፈላጊውን የማማከር ሥራ ይሠራሉ፣ በጽሁፍ አዘጋጅቶ ያቀርባሉ፤
O ሀላፊው ዓላማ ለመደገፍ የሚችሉ የልማት ፕሮጀክቶች ስምምነቶች ከመፈረማቸው በፊት ከመንግስት ፖሊሲ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው፣ ቴክኒካዊ ብቃታቸውና የሚያበረክቱት ጥቅም በመገምገም እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር በመመካከር የውሳኔ ሀሳብ በማቅረብ ሀላፊው ያማክራሉ፤
O ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች/አካላት ጋር በመተባበር በውይይት/ወርክ ሾፕ/ ሴሚናር/ መድረኮች ላይ መቅረብ የሚገባቸውን ጉዳዮች አጠናቅሮ ያቀርባሉ፤
O የሥራ ክፍሎች እቅድ ተጣጣሚነት ያለው ሆኖ እንዲዘጋጅ፣ እንዲተገበርና የአፈጻጸም ውጤታማነቱም ወጥነት እንዲኖረው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ይሠራሉ፤
O በክልሉ ውስጥ ካሉ የየግብርና መስሪያ ቤቶች መካከል ጤናማ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ፣ ተደጋጋፊ የሥራ ግንኙነት እንዲፈጠር ለማድረግ የሥራ ሂደቶች በሚያቀርቧቸው ጥናቶች ወይም ንድፈ ሃሳቦች ላይ ሙያዊ አስተያየት በመስጠት ያቀርባሉ፣
O ከመ/ቤቱ፣ ከተጠሪ ተቋማት፣ ከባለድርሻ አካላትና ተገልጋዮች የሚቀርቡ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ከመንግስት ፖሊሲና የልማት አቅጣጫ አንጻር እያጠና የፖሊሲ ትንታኔና ማብራሪያዎች ያዘጋጃሉ፤
O በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከሀላፊ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ ጥናት፣ ማብራሪያ ወይም ምላሽ አዘጋጅተው ያቀርባሉ፤
O በተቋሙ አሠራርና አስተዳደር ዙሪያ የተጻፉ ወቅታዊ ጽሁፎችን፣ በመተንተን እና ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ሊሻሻሉ ወይም ሊለወጡ የሚገባቸው አሠራሮች ወይም አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየትና የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባሉ፤
O አግባብ ካላቸው ሙያተኞች ጋር በመተባበር የተቋሙን ተልዕኮ በሚመለከት የሚደርጉ የሁለትዮሽ/ሶስትዮሽ ግንኙነት፣ የመግባቢያ ስምምነት ላይ ተገቢውን ጥናት በማድረግ ስምምነቱ ከመፈረሙ በፊት የተዘጋጀውን ሰነድ በመመርመር ሀላፊው ያማክራል፣ ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጋር በመሆን የስምምነት ሰነድ አዘጋጅተው ያቀርባሉ፤
O የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር አኳያ ለሚስተዋሉ ቁልፍ የህብረተሰቡን ችግሮች መነሻ ወይም መንስኤ የሆኑ የአሠራር ሥርዓትና የሕግ ክፍተቶችን በመፈተሽ ችግሮቹን ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ ሃሳቦችን ያቀርባሉ፤
O በሥራ የግብርና ልማት፣ አሰራርና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከተገልጋይ ኅብረተሰብ፣ ከባለድርሻ አካላት እና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ከሚደረጉ ውይይቶች እንዲሁም በሌሎች የተለያዩ መንገዶች የሚገኙ መረጃዎችን በመጠቀም ቁልፍ ችግሮችን በመለየት የመፍትሔ ሀሳቦችን ያቀርባል፤
O ተቋሙን በመወከል በፎረሞች፣ ሴሚናሮችና መድረኮች ላይ ይገኛሉ፤
O በተቋሙ የሚከናወኑ ቴክኒካል ጥናቶችን ወይም ንድፈ ሀሳቦች ላይ ሙያዊ አሰተያየት በመስጠት ያማክራሉ፣
O በተቋሙና በየግብርና የሚወጡ ህጎችን፣ ፖሊሲዎችን፣ ፕሮግራሞችንና ዕቅዶችን በመገምገም ችግሮች በጥናት እንዲለዩና የመፍትሄ ሀሳብ ያቀርባል/ እንዲቀርብ ያደርጋሉ፣
O የተቋሙን/ የግብርናን የአደረጃጀትና የአሰራር ሥርዓት እንዲሻሻል በጥናት የተደገፉ ሀሳቦችን ያቀርባል፣
O በተቋሙ የተዘጋጁ የጥናት- ምርምር የፕሮጀክት ሰነዶችን ይገመግማል፣ ሙያዊ አስተያየት ያቀርባሉ፤
O ከባለጉዳዮች/ከተገልጋዮች የተቋሙን የበላይ ኃላፊ ቀርበው የተመሩለትን ማመልከቻዎች ከድንብና መመሪያዎች ጋር በማመሳከር ለውሳኔ ከሚረዳ አስተያየት ጋር ያቀርባል፣ በጉዳዩ ላይ ያማክራሉ፤
O ለወደፊቱ ተመሳሳይ ቅሬታዎችና ተመሳሳይ ጉዳዮች በውሳኔው መሰረት ተፈጻሚ እንዲሆኑ ፈጻሚ አካላት እንዲያውቋቸው ያደርጋሉ፤
O ውሳኔ የተሰጠባቸውን ቅሬታዎችና ጉዳዮች በተመለከተ መረጃዎችን አደራጅቶ በመያዝ ለስልጠና እና ለጥናት ሥራዎች በግብዓትነት እንዲውሉ ያደርጋሉ፤
O በተቋሙ አሰራር ዙሪያ ከሌሎች የሥራ ከፍሎች ጋር በመቀናጀት የተገልጋዮችን ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚያስችል ሥልጠና ይሰጣሉ፤
O ሥራው የሚመራበትን ዕቅድና ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባሉ።
O የጽ/ቤቱን ዓመታዊ ዕቅድ እንዲሁም በአፈጻጸም ሂደት የሚያስፈልግ በጀትና ግብዓቶች የዕቅድ አካል ተደርገው መዘርዘራቸውን ይከታተላል፣
O የተቋሙን ተልዕኮ ከማሳካት አንጻር ችግሮችን ይለያል፣ መፍትሔ እንዲያገኙ ተገቢውን ክትትል ያደርጋል፣
O የዕቅድና ፕሮግራም ክንውን እና አጠቃላይ የበጀት አጠቃቀምን አስመልክቶ አፈጻጸሙን በጋራ ይገመግማል፣
O ጽ/ቤቱን አስመልክቶ በየጊዜው ለበላይ አካላትና ለተለያዩ መ/ቤቶች የሚቀርቡ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረባቸውን ይከታተላል፣
O የደጋፊ ስራ ክፍሎች የሥራ አፈፃፀም በየምዕራፉ ይገመግማል፣ የተጠቃለለ የምዘና ሪፖርቶችን ያቀርባል፣
O በሥራ ክፍሉቹ ውስጥ የታታሪነት ስሜትና ተነሳሽነት እንዲፈጠር በዘላቂነትም እንዲቀጥል ተገቢውን አመራር ይሰጣል፣
O በሥራ ክፍሉቹ የሚገኙ ልዩ ልዩ ሰነዶችን በአግባቡ ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ ሆነው እንዲደራጁ ያደርጋል፣
O በበላይ አመራሩ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችን ከህግና መ/ቤቱ ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት አንፃር በመለየት በማስረጃ ተደግፈው እንዲቀርቡ ያደርጋል፣ ተፈጻሚነታቸውም ክትትል ያደርጋል፣ ውጤቱንም ለአመራሩ ያቀርባል፣
O ከሥራ ዘርፎች፣ ከተጠሪ ተቋማት እንዲሁም ከውጪ ለቢሮ ሀላፊው የሚላኩ ጉዳዮችን በማየት በራሱ ለሚፈጸሙት ምላሸ ይሰጣል፤ የቢሮ ሀላፊ ውሳኔ የሚሹትን ለዋና ሀላፊ ያቀርባል፤
O ለተለያዩ አካላት የሚጻፉ መልዕክቶችንና ደብዳቤዎችን አዘጋጅቶ ለቢሮ ሀላፊ ያቀርባል፣
O ከበላይ አመራሩ ወደ ተለያዩ የሥራ ክፍሎች የሚመሩ ደብዳቤዎችንና ልዩ ልዩ ጉዳዮችን በተሰጠው ውክልና መሠረት መፈጸሙን ይከታተላል፡፡
O ወጪ የሚሆኑ ደብዳቤዎችን፣ ሰርኩላሮችንና መመሪያዎችን ለሚመለከታቸው አካላት መሰራጨታቸውን ያረጋግጣል፡፡
O የህግ ነክ ጉዳዮች አገልግሎት አሰጣጥ ዕቅድ ዝግጅትና ትግበራ በበላይነት ይመራል፣ ይቆጣጠራል።
O በመ/ቤቱና በሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚደረጉ የፕሮቶኮል ስምምነት ሰነዶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣ ያስፈጽማል፣
O የማኔጅመንት ስብሰባዎች የሚመሩበትን መርሃ-ግብር አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መድረኮቹ እንዲካሔዱ ያደርጋል፣ የተሰጡ ውሳኔዎችን እና አቅጣጫዎችን ተፈጻሚነት ይከታተላል፣
O በበላይ አመራሩ ሰብሳቢነት ለሚካሄዱ ስብሰባዎች አጀንዳዎችን በመለየት አዘጋጅቶ ለተሰብሳቢዎች እንዲበተን ያደርጋል፤ የስብሰባ ቃለ ጉባኤዎችን ይይዛል ወይም እንዲያዝ ያደርጋል፣ ቃለጉባኤውን በቼክ ሊስት አዘጋጅቶ ለሥራ ክፍሎችና ለሚመለከታቸው አካላት ይልካል።
O የበላይ አመራሩ ለሚካፈሉባቸው ብሔራዊ ስብሰባዎች የሚያስፈለጉ መረጃዎችንና መግለጫዎችን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ተጠናቅረው እንዲቀርቡ ያደርጋል፣
O የተቋሙ ተልዕኮ ውጤታማ እንዲሆን ከሚመለከታቸው የውስጥና የውጭ አካላት ጋር ግንኙነት ያደርጋል፣ ይደግፋል፣
O የአደረጃጀትና የአሰራር ሥርዓት እንዲሻሻል የተለያዩ ልምዶችና ነባራዊ እውነታዎች ተዳሰው የሚቀመሩበትንና ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማዛመድ ምርጥ ተሞክሮዎችን ይቀምራል፣ ያስፋፋል።
O ከስሩ ከታች የተዘረዘሩ የስራ ክፍሎች ያስተባብራል፡-
o. የልማትና በጀት እቅድ ዝግጅት ክ/ግ/ግ ዳይሬክቶሬት
o. የግብርና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
o. የኦዲት ዳይሬክቶሬት
o. የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት
o. የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
o. የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት
o. የግዥ ዳይሬክቶሬት
o. የጋራ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
o. የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዩች አካትቶ ትግበራ
o. የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU