CERS-Bureau of Agriculture
የ3 በ 7 የማር ልማት ፕሮጀክት /(3 ዘመናዊ 7 ባህላዊ ቀፎ ለአንድ ቤተሰብ)/፡
ይህ ፕሮጀክት የ30-40-30 አካል ሆኖ አንድ ቤተሰብ በትንሹ ሶስት ዘመናዊ ቀፎና ሰባት ባህላዊ ቀፎ እንዲኖረው ታቅዶ እየተተገበረ ነው። የንብ ሀብት ልማት በአነስተኛ ገንዘብ የሚካሔድና በማንኛውም የዕድሜ ክልል ያለ ሴትም ሆነ ወንድ አርሶ አደር ወይም የከተማ ነዋሪ ሊሰራው የሚችለው የቤተሰብ ግብርና ተግባር ከመሆኑ በተጨማሪ በባለሀብቶችም በስፋት ሊከናወን የሚችል ስራ ነው፡፡ ልማቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምርት የሚሰጥና አነስተኛ የመሬት ይዞታ ባላቸው የህብተረሰብ ክፍሎችም በስፋት ሊሰራ የሚችል በመሆኑ ድህነትን ለመቀነስ የሚረዳ ሲሆን ባለፉት ሁለት አመታት በኢኒሺዬቲቩ በታቀደው አሰራር መሰረት የተተገበረና እየተተገበረ ሲሆን በተመረጡ 24 መንደሮች 340 የጨፈቃ ቀፎ፣ 478 የሽግግር (ኬንያ) ቀፎና 422 የባለፍሬም ቀፎ በማሰራጨት 341 አባወራ 210 እማወራ፣ 296 ወጣቶችና ሴቶች በድምሩ 647 አናቢዎች ተሳታፊም ተጠቃሚ የሆኑበት ሲሆን ይህ ጅምር ውጤት በቀጣይ በላቀ ትኩረት ለማስፋት እንደ መነሻ የሚሆን ውጤት ነው፡፡
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU