• Call Us
  • +25146 554 16 87

የ 10 በ25፤ 20 በ 25ሜ እና 20 በ 50ሜ የተሻሻለ የመኖ ልማት ፕሮጀክት

                   የ10 25, 20 25 እና 20 50 የተሸሻለ መኖ ልማት ፕሮጀክት፡

100ካሜ፣ 250 ካሜ፣ 500 ካሜ፣1000 ካሜ በሆነ ማሳ በቤተሰብ ደረጃ በተሻሻለ መኖ ልማት በመሳተፍ የእንስሳት መኖ አቅርቦት ለማሳደግ ማልማት ነው። ይህ ማለት አንድ ቤተሰብ ከሶስቱ አማራጮች እንደአቅሙ አንዱን ተጠቅሞ ያለማል። ማለትም (250 ካሜ፣ 500 ካሜ እና 1000 ካሜ) የእንስሳት መኖ በቤተሰብ ደረጃ የማልማት ኢኒሼቲቭ ነው። በተመሳሳይ ይህ ፕሮጀክት አንድ ቤተሰብ በትንሹ ከአንድ እስከ ሁለት የተሻሻለ የወተት ዝርያ ጊደር/ላም የሚኖረው ሲሆን ይህ ፕሮጀክት ለአንድ ቤተሰብ 250 -1000 ካሜ ቦታ መኖ ያለማል ማለት ነው። መኖ ለእንስሳቱ እና ለአልሚው ቢዝነስና ገቢ ብሎም ስራ እድል ጭምር መፍጠሪያ እንዲሆን ተቀርፆ እየተተገበረ ያለ ፕሮጀክት ነው። እስካሁን በርካታ ውጤቶች የተመዘገበበት ኢኒሼዬቲቭ ሲሆን 2015/6 / በበልግና መኸር ወቅት 234,334 አርሶ አደሮች በቤተሰብ ደረጃ ኩታገጠም በሆነ መልኩ 250 -1000 ካሜ መሬት የተለያዩ ማልሚያ ስልቶች ተጠቅሞ እንዲያለማ በመደገፍ 106,277 / መሬት በመሸፈን ተደማሪ ውጤትና ስኬት እንዲመጣ ያደረገ ኢኒሺዬቲቭ ነው፡፡ በተመሳሳይ የመንግስትና የግል ተቋማት በመኖ ልማት እንድሳተፉ በማድረግ 354 ትምህርት ቤቶች 531/ መሬት መኖ እንዲያለሙ በማድረግ፣ በክልሉ በተገነቡ በመስኖ አወታሮች ከሰብል ልማት ጋር በማቀናጀት 200 / ማሳ በማልማት  የመኖ ሽፋን እንዲሰፋና አቅርቦቱ በማሳደግ የእንስሳት ተዋፅኦ ምርት እድገት ላይ የማይናቅ አስተዋፅኦ እያደረገ ያለ ውጤታማ ስልት ነው፡፡