CERS-Bureau of Agriculture
የክልሉ አጠቃላይ ገፅታ ከግብርና አንጻር
ባለፉት ዓመታት በሀገራችንም ሆነ በክልላችን በተካሄደው የለውጥ እንቅስቃሴ ህዝቡ በየደረጃው የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በተጠናና በተደራጀ መልክ ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠት አስፈላጊ በመሆኑ እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፌዴሬሽን ም/ቤት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በክልልነት እንዲደራጅ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ቀሪው የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ ነባር ክልል ሆኖ ስያሜውን በመቀየር እዲቀጥል ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ክልሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስያሜውን በመቀየር በአዲስ መልክ ተዋቅሯል፡፡
የማእክላዊ ኢትዮጵያ ክልል በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት በአዋጅ ቁጥር 1/1987 ዓ.ም. አንቀጽ 47 መሠረት በ2016 ከተመሰረቱት ክልሎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ክልሉ የሚገኘዉ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ አቅጣጫ ሆኖ በሰባት ብዝሀ ማዕከላት የተዋቀረ ነው፡፡ የክልሉ ርዕሰ ከተማ ሆሳዕና ከተማ ሲሆን የግብርና ቢሮ ማእከል ዱራሜ ከተማ ነው፡፡
o የክልሉ መገኛ ቦታ ከ70 04’ እስከ 80 03’ ሰሜናዊ ኬክሮስና ከ370 20’ እስከ 380 60’ ምሥራቃዊ ኬንትሮሰ ላይ ነዉ፡፡ አዋሳኞችም በሰሜን በምእራብና በምስራቅ አቅጣጫ ከኦሮሚያ ክልል እና በደቡብ በኩል ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በደቡብ ምዕራብ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ይዋሰናል፡፡ አስተዳደራዊ መዋቅሩም በዞን ፣ በልዩ ወረዳ፣ በወረዳ፣ በከተማ አስተዳደሮች እና በቀበሌዎች የተደራጀ ነዉ፡፡
o ክልሉ 15,156 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ የቆዳ ስፋት 1.38 በመቶውን ይይዛል። የሕዝብ ብዛት በተመለከተ በ1999 ዓ.ም.የብሔራዊ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት መረጃ ፕሮጀክሽን መሠረት የክልሉ የሕዝብ አማካይ አመታዊ ዕድገት ምጣኔ 2.9 በመቶ ነው። የሕዝብ ዕድገት ምጣኔ በገጠር ሕዝብ አመታዊ ዕድገት በ2.8 በመቶ ሲሆን በከተማ 4.8 በመቶ ነዉ። በዚህ መሰረት በ2015 ዓ.ም. የክልሉ ሕዝብ 7,039,772 እንደሆነ የሚገመት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 80.7% በገጠር እና ቀሪው 19.3 % በከተሞች የሚኖር ነው፡፡ ይህም ከአገሪቱ አጠቃላይ ህዝብ 6.47 በመቶውን ይይዛል። የክልሉ አማካይ የህዝብ ጥግግት 464 ሰዎች በካሬ ኪ.ሜ ነው፡፡
o ክልሉ በአሁኑ ወቅት በ7 ዞኖች፤ በ50 ወረዳዎች፤ በ3 ልዩ ወረዳዎች እና በ29 የከተማ አስተዳደሮች የተከፈለ ነው። በክልሉ1,310 የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች ያሉት ሲሆን ከነዚህም 178 የከተማ እና 1,132 የገጠር ቀበሌያት ናቸው፡፡
o የማዕክላዊ የኢትዮጵያ ክልል በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የአየር ንብረቶች ይዟል፡፡ የክልሉ ከፍተኛ ሥፍራ ከባህር ጠለል በ3,721 ሜትር ከፍታ ያለው በጉራጌ ደጋ ዘቢደር ተራራ ጫፍ ሲሆን ዝቅተኛው ሥፍራ በጠምባሮ ልዩ ወረዳ በኦሞ ወንዝ አቅራቢያ ባለው የኦሞ ሸለቆ ጫፍ ከባህር ጠለል በላይ ወደ 447 ሜትር ከፍታ ያለው ሥፍራ ነው፡፡
o በእነዚህ ሁለት የተለያዩ ጫፎች መካከል የሚገኙ የክልሉ አካባቢዎች ለኑሮ ምቹ የሆኑ የደጋ፣ የወይና ደጋ እና የቆላ አከባቢዎች አሉት፡፡ ይህ በሁለት የተራራቁ ጫፎች ያለው የአየር ንብረትም በክልሉ የተለያዩ ስነ-ምህዳር (ecology) የተፈጥሮ ሀብቶች፣ የተለያዩ የግብርና ሥርዓቶች ፣ የአኗኗርና የባህል ብዝሀነት እንዲኖር አድርጓል፡፡
o ክልሉ ዋነኛ የኢኮኖሚ መሰረት ብዝሀነት ያለው የግብርና ሥርዓት (diversified agricultural systems) ነው፡፡ በክልሉ የግብርና ሥርዓት ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የእርሻ ሥራ ሲሆን የእንስሳት እርባታም ጎን ለጎን ይካሄዳል፡፡ በክልሉ በዋነኛነት የሚመረቱ የብርዕና አገደ ሰብሎች (በቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍ)፤ ጥራጥሬ (አተር፣ ባቄላ)፤ የተለያዩ ፍራፍሬዎች (ሙዝ፣ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ አፕል፣ አናናስ)፤ የስራ ስር ሰብሎች (እንሰት፣ ድንች፣ ጎደሬ)፤ እንዲሁም ቡና፤ ዝንጅብል እና የተለያዩ ቅመማ-ቅመሞች ወዘተ ናቸው፡፡
o በ1999 ዓ.ም. የብሔራዊ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ዉጤት መረጃ ትንቢያ ፕሮጀክሽን መሠረት የክልሉ የሕዝብ አማካይ አመታዊ ዕድገት ምጣኔ 2.9 በመቶ ነው። የሕዝብ ዕድገት ምጣኔዉ በመኖሪያ አካባቢ በተመለከተ የገጠር ሕዝብ አመታዊ ዕድገት በ2.8 በመቶ ሲሆን በከተማ የሕዝብ የዕድገት ምጣኔ 4.8 በመቶ ነዉ ። በመሆኑም በ1999 ዓ.ም. የብሔራዊ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ዉጤት መረጃ ትንበያ መሠረት በ2015 ዓ.ም. የክልሉ ሕዝብ 7,039,772 የደረሰ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 80.7% በገጠር የሚኖር ሲሆን ቀሪዉ 19.3 % በከተሞች የሚኖር ነዉ ።
o የክልሉን የመሬት የቆዳ ሰፋት መሰረት በማድረግ አማካይ የሕዝብ ጥግግት በካሬ ኪሎሜትር 464 ሰዎች በካሬ ኪሎ ሜትር የሚኖሩ ሲሆን በጣም ብዙ ህዝብ ከሚኖርባቸው የክልሉ ዞኖች ውስጥ የከምባታ ዞን 828 ሰዎች በካሬ ኪሎ ሜትር ፣ ሀዲያ ዞን 560 ሰዎች በካሬ ኪሎ ሜትር ፣ ጉራጌ ዞን 351 ሰዎች በካሬ ኪሎ ሜትር ሲሆኑ ዝቅተኛው የህዝብ ብዛት በየም ዞን 200 ሰዎች በካሬ ኪሎ ሜትር ነው፡፡
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU