• Call Us
  • +25146 554 16 87

የ2017 የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ የብረተሰቡ ተሳትፎና መነሳሳት፣ የስራው ጥራትና መጠን እየጨመረ መጥቷል::

2017 የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ የብረተሰቡ ተሳትፎና መነሳሳት፣ የስራው ጥራትና መጠን እየጨመረ መጥቷል ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ዑስማን ሱሩር ገለጹ፡፡

ቢሮ ኃላፊው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የተጎዱ መሬቶች፣ የተራቆቱ ተራሮች፣ በደለል እየተሞሉ የነበሩ ግድቦች፣ሀይቅና ወንዞችን፣ የአፈር ለምነት መመናመንን ከአደጋ በመከላከል ለዚህ ትውልድ ተጠቃሚነት፣ ለቀጣዩ ትውልድ ዘላቂነትና ውብ፣ ለምና ምርታማ መሬት ማቆየት አይነተኛ መፍትሄ የሆነውን የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ በህብረተሰቡ ተሳትፎና ባለቤትነት በመሰራቱ ተጨባጭ ውጤት መጥቷል ብለዋል፡፡

በውጤቱም ህብረተሰቡ መጠቀም በመጀመሩ ስራው ባህል እየሆነ መጥቷል ያሉት አቶ ኡስማን በዘንድሮው ስራ የሴቶች፣የወጣቶች፣ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተሳትፎ እጅግ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዘንድሮው ልዩ የተቀናጀ ተፋሰስ ስራ ጥራት ጨምሯል፣ ተሳትፎ አድጓል፣ ባለቤትነት ጎልቶ ታይቷል፤ ፍጥነትና ብዛት ጨምሯል ሲሉ ተናግረዋል።

እነዚህ የዘላቂነት ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰው በዚህ አመት ንቅናቄ የህብረተሰቡ ተሳትፎና መነሳሳት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያን የመበልፅግ ተስፋ የሚያለምልም ነው ሲሉም አመልክተዋል፡፡

"ግብርናችን የመበልፀግ ተስፋችን"!