• Call Us
  • +25146 554 16 87

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በግብርናው ሴክተር በሁሉም ዘርፎች የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል::

የክልሉ ግብርና ሴክተር 2017 1 ሩብ ዓመት የዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተጠናቋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ኡስማን ሱሩር በመድረኩ ማጠቀለያ ላይ እንደገለጹት የሩብ ዓመቱ አፈጻጸም በግብርናዘርፍ ለማሳካት ያስቀመጥናቸው ግቦች ትክክለኛ ሀዲድ ላይ መሆናቸውን ያሳያል ብለዋል፡፡

ግብርናን አዘምነን የህብረተሰባችንን ተጠቃሚነት እናረጋግጠለን ብለን የጀመርነው ተስፋ ወደ ሚጨበት ተስፋ ብርሃን እየተቀየረ መሆኑን ያመላከቱት ቢሮ ኃላፊው ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን፣ገበያ ማረጋጋት፣ ለአምራች አርሶአደሮች የተሻለ ገቢ መፍጠር፣የሞቱና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ መሬቶች ወደ ምርታማት መቀየራቸውን እንዲሁም በሁለም መዋቅሮች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባህል ተቀራራቢ እንዲሆን ከማድረግ አንጻር የተሻለ አፈጻጸም መኖሩን ገልጸዋል፡፡

በኢኒሼቲቮች ትግበራ የብሮው ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አይተኬ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

አቶ ኡስማን አያይዘውም በሩብ ዓመቱ በግብርናው ሴክተር በሁሉም የተሻለ ውጤት መመዝገቡን አብራርተው ለውጤቱም ከክልል እስከ ታችኘው መዋቅር ያለው አካል በተናበበ፣ በተቀናጀና በተባበረ ጥረት ነው ብለዋል፡፡

በሩብ ዓመቱ የተገኙ ስኬቶችን ማጽናትና ማነቆዎችን መፍታት ከሁሉም አካላት ይጠበቃል ያሉት አቶ ኡስማን ለዚህም ሁለችንም በተቀራራቢ የአስተሳሰብ ደረጃ ላይ መምጣት አለብን ብለዋል፡፡

በመድረኩም የሁሉም ዘርፎችና ተጠሪ ተቋማት የሩብ ዓመቱ ሪፖርት ቀርቦ ጥልቀት ያለው ውይይት ተደርጓል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሪፖርቶቹ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ክቡር አቶ ኡስማን ሱሩር ምላሽና ማብራሪያ በመስጠትና ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል፡፡