• Call Us
  • +25146 554 16 87

ከገንዘቡ በላይ ውህደታችንን፣

ህዳር 16/2016

ከገንዘቡ በላይ ውህደታችንን፣ አንድነታችን ትልቅ ትርጉም ያለው ነው- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው

የክልሉ ተወላጅ ባለሀብቶች ለክልሉ 330 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር ድጋፍ አደረጉ

ባለሀብቶች ለየአካባቢያቸው ሁለንተናዊ ልማት ከሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ በላይ ለህብረተሰቡ ውህደትና አንድነት የሚያሳዩት ቁርጠኝነትና አብሮነት ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ተናገሩ።

አቶ እንዳሻው በክልሉ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ማጠቃለያ ላይ አንድ ሆነን የማናሸንፈው ችግር፣ የማንወጣው ዳገት የለም ብለዋል።

የህዝብን አቅም በአግባቡ ማሰባሰብ ከቻልን ታሪክ እንሰራለን ሲሉም ጠቁመዋል

ክልሉን ሰላም የሰፈነበት፣ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በእኩልነት የሚኖሩበትና ሁሉም ሀሳቦች የሚስተናገዱበት በማድረግ በኩል በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል

ሀገራችን ኢትዮጵያን ትልቅ ለማድረግ በጋራ እንሰራለን ያሉት አቶ እንዳሻው በእነዚህ የለውጥ ስራዎቻችን ከጎናችን ሆናችሁ እንድታግዙን እንጠይቃለን ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል

በዛሬው እለት አዲስ አበባ ስካይ ሆቴል በተካሄደ የክልሉ ገቢ ማሰባሰቢያ ከባለ ሀብቶች፣ከዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በድምሩ 330 ሚሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን ገንዘቡ መልሶ የህዝብ ልማት የሚካሄድበት መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል