CERS-Bureau of Agriculture
የእንስሳት ሀብታችን ለብልጽግናችን! በሚል መሪ ቃል ክልላዊ የዶሮ ሀብት ልማት የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ኡስማን ሱሩር እንደገለፁት የዶሮ ሀብት ልማት ለወጣቶችና ለሴቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር ለኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ቁልፍ ሚና ይጫወታል።
በበለፀጉት ሀገራት ዶሮና የዶሮ ውጤቶች ዋጋ በንፅፅር ርካሽ ሲሆን በሀገራችን ግን እጅግ ውድ ሆኖ ይስተዋላል ያሉት የተከበሩ አቶ ኡስማን የዚህ ምክንያቱ ሀብቱን በአግባቡ አለማልማታችን እንደሆነ ገልፀዋል።
ይህንን ሁኔታ ለመቀየር እንዲቻል የዘርፉ ልማት ማነቆዎችን ከባለድርሻዎችና አጋሮች ጋር በመቀናጀት መሥራት ይገባል ያሉት ደግሞ የክልሉ ዶሮ ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ደስታ ገብርኤል ናቸው።
በክልሉ የሚገኘውን ሰፊ የዶሮ ሀብት አልምቶ በመጠቀም የሥርዓተ-ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የሥራ ዕድልን ለመፍጠር፣ የኅብረተሰብ የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ከድህነት ለመውጣት አስተዋፅዖ ስለሚያበረክት ለዘርፉ ልማት መፋጠን የዘርፉ ልማት አካላት ተቀናጅተው ሊረባረቡ እንደሚገባ መገለፁን የቢሮው የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዘግቧል።
መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም
ቡታጅራ
Copyrights 2025. . Centeral Ethiopia Bureau of Agriculture. All Rights Reserved.
Developed by CE-SCIENCE AND INFORMATION TECHNOLOGY BUREAU