• Call Us
  • +25146 554 16 87

የሌማት ትሩፋትን እውን ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡

የሌማት ትሩፋትን እውን ለማድረግ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን ተገለፀ

ሕዳር 17/2016 /

#በማዕከላዊ_ኢትዮጵያ_ክልል_በስልጤ_ዞን_ስልጢ_ወረዳ_መናኻሪያ_01_ቀበሌ ላይ #በማህበር_ተደራጅተው__1_ቀን_ጫጩት ማሳደግ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች እየሰሩ ያሉትን ስራ የመስክ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት ላይ ነው።

ከኮሌጅና ከዩንቨርሲቲ ተመርቀው ወጣቶች በዚህ መልክ በሌማት ትሩፋት ስራ ተደራጅተው መስራታቸው እጅግ አበረታችና አስደናቂ መሆኑና ተሞክሮም ሊቀመርበት የሚገባ ትልቅ ስራ መሆኑን የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር ገልፀዋል።

አሁን ያለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋገት ወሳኝ መሆነን በማንሳት በማህበሩ የተደራጁ ወጣቶች በቀጣይ በስፋት ሰርተው ለሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከሀገር ውጭም ኤክስፖርት መድረግ እንደሚችሉ በማንሳት የማህበሩ ውጤት ከዚህ በላይ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እናደርጋለንም ብለዋል።

በመስክ ምልከታው መርሃ-ግብር ንግግር ያደረጉት የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ቀድሩ አብደላ ከሌማት ትሩፋቶች አንዱ የሆነው የዶሮ ማርባት ስራ በስልጢ ወረዳ በመናኻሪያ 01 የተጀመረው እጅግ የሚያስደስት መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ ማህበሩ አሁን ባለበት ደረጃ ተጠናክሮ ቀጥሎ እንደ ጅምሩ ሁሉ እስከ መጨረሻው በጋራና በመግባባት በጥንካሬ በመስራት እራሰቸውን ቤተሰቦቻቸውን ብሎም የወረደውን ህብረተሰብ ሊላውጡ እንደሚችሉ ኃላፊው አብራርተዋል።

እንደ ወረዳ ማህበሩን አሁን ላለበት ደረጃ ለማድረስ የተለያዩ ድጋፍና ክትትል መደረጉንና ማህበሩም ከሚያስገኘው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የአርሶ አደሩን የግባት ችግር መቅረፍ፣ስረ ዕድልን መፍጠር፣ኑሮ ማረጋጋት ላይ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የዶሮ መንደር በመመስረት ከማህበሩ ጋር በማስተሳሰር ትኩረት ተደርጎ እና ተለይቶ እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር ደድገባ አስታውቀዋል።

በዶሮ እርባታ ስራ በማህበር ተደራጅተው የተሰማሩ የመነሀሪያ 01 ቀበሌ ወጣቶች አባላቱ በተሰማሩበት የስራ መስክ ላይ ሌተቀን እየሰሩ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የዶሮ እርባታ ስራ በዲግሪና ዲፕሎማ የተመረቁ ወጣቶቹ ተደራጅተው በዚህ መልክ የዶሮ እርባታ ስራ ላይ ለመሰማራት ወረዳው የጀመረውን በተማረ ሀይል ስራውን ለመስራት በቀረበው ፕሮፖዛል መሰራት በተሰጠው ስልጠና ወደ ስራ መገባቱንም ገልፀዋል።